በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሣሾች 1ኛ ቻላቸው አለነ፣ 2ኛ ምሳየ መላኩ፣ 3ኛ የቤቴ አሳየ ወራሽ አያል ፋሪስ፣ 4ኛ አለነ ቢያድግልኝ፣ 5ኛ ቄስ መላኩ እባቡ እና 6ኛ አሳየ ቢያድግልኝ፣ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የ5ኛ አፈፃፀም ተከሳሽ የቄስ መላኩ እባቡ የሆነውን ቤት በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ቀበሌ 01 በምሥራቅ ቄስ መላኩ እባቡ፣ በምዕራብ አብራሬ፣ በሰሜን መንገድ እና በደቡብ የእግር መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው በግምቱ ብር 662,842.91 /ስድስ መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሁለት ብር ከዘጠና አንድ ሳንቲም/ በሃራጅ ጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሙጃ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኝት መግዛት ወይም መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ሃያ አምስት በመቶ ለሐራጅ ባይ ወዲያውኑ የሚያስረክብ ሲሆን ቀሪው ክፍያ ህጉ በሚደነግገው እና የፍ/ቤቱ ችሎት በሚያዘው መሰረት ለፍርድ ባለሀብቱ አጠቃሎ የሚከፍል መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት