በአፈ/ከሳሽ ሰማኸኝ አዘነ እና በአፈ/ተከሳሽ ሙሉሃብት ገብሬ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በአፈ/ተከሳሽ ሙሉሃብት ገብሬ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ፤ካርታ ቁጥር 12544 /2015 በሰሜን እና በምስራቅ መንገድ ፣በደቡብ ደጉ ሙሉ ፣ በምእራብ ደግነት አለኸኝ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው እና 200 ካ.ሜ የሆነ ቤት በመነሻ ዋጋ 1‚774‚488.26 /አንድ ሚሊዩን ሰባት መቶ ሰባ አራት ሽህ አራት መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከሀያ ስድስት ሣንቲም/ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ፤ በሰአቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ ሲሆን ፤ የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን 1/4ኛውን ወዲያውኑ በሞ/85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳርና አካ/ከ/ፍ/ቤት