በአፈ/ከሣሾች —- 1ኛ አቶ ጉበና አባተ 2ኛ አቶ መሀመድ ዘይን ጠበቃ ሀይልየ በሪሁን እና በአፈ/ተከሣሾች 1ኛ ወ/ሮ ዘይነቡ አባተ ፣1.2 ወ/ሮ ራቢያ አስፋውና 1.2 ህፃን ፊሊጶስ አስፋው ሞግዚት ህይወት ካሳው 2ኛ ወ/ሮ ዘሀቡ ኣባተ መካከል ሥለለው የገንዘብ አፈፃጸም ክርክር ጉዳይ በመርሳ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሸል እየተባለ ከሚጠራ ስፍራ በምሥራቅ የመኪና መንገድ ፣በምዕራብ መንገድ በሰሜን የአቶ መብራቱ ሱልጣን ወራሾች እና በደቡብ የአቶ አሊጋዝ ሲሳይ ወራሾች ከሚያዋስኑት 391.07 (ሶስት መቶ ዘጠና አንድ ነጥብ ሰባት) ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተሰራ 03 /ሶስት/ የድርጅት የቆርቆሮ ክዳን ቤት 08 (ስምንት) የቆርቆሮ ክዳን ሰርቪስ ቤት 02 (ሁለት) ክፍል የቆርቆሮ 2 /ሁለት/ ክፍል የቆርቆሮ ክዳን ሽንት ቤትና ኩሽና ቤት በብር 3,057,306.85 /ሶስት ሚሊዮን አምሳ ሰባት ሽህ ሶስት መቶ ስድስት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም/ መነሻ ዋጋ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከሚያዚያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ጨረታው ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ ንብረቱ በሚገኝበት መርሳ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሽል ከተባለው ቦታ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የጨረታ አሸናፊው የአሸነፈበትን 1/4 ኛውን ለፍርድ ቤቱ ሐራጅ ባይ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የሰ/ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት