በአፈ/ከሳሽ መልካሙ ሽታው እና በአፈ/ተከሳሽ አዳነ ውዱ መካከል ስላለው አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፄ ቴወድሮስ ክ/ከተማ ማራኪ ቀበሌ በካርታ ቁጥር 46049/2013 በአፈ/ተከሳሽ አዳነ ውዱ ስም ተመዝግቦ የሚገኝውን በአዋሳኝ በምሥራቅ ፣በምዕራብ እና በደቡብ የግለሰብ ቤት እንዲሁም በሰሜን መንገድ ተዋስኖ የሚገኘውን 100 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,453,426 (ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ አምሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሃያ ስድስት ብር) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ የፍ/ቤቱ ሃራጅ ባይም ጨረታው በሚካሄድበት በአፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ማራኪ ቀበሌ ንብረቱ በሚገኝበት በመገኘት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በዕለቱ ጨረታውን ያሸነፈ ያሸነፈበትን 1/4 ኛውን በሞ/85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚያዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከ/ፍ/ቤት