የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
76

በአፈ/ከሳሽ ዘኪያ ኑርየ ጠበቃ ማቲያስ መርእድ እና በአፈ/ተከሳሽ ሮዚያ ኑርየ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በወልድያ ከተማ 05 ቀበሌ ሙጋድ ከተባለው ልዩ ቦታ በአዋሳኙ በምሥራቅ መንገድ ፣ በሰሜን እና በደቡብ መንገድ ፣ በምዕራብ መህቡባ መካከል ከሚገኘው 300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያለው ስምንት ክፍል ፎቅ እና ምድር ቤት ፣ከዚሁ ላይ ያለ አንድ ክፍል ቤት ከነጭስ ቤቱ ፣አራት ክፍል ቤት ከነጭስ ቤቱ እንዲሁም ከነዚህ ውጭ ያሉ ሁለት ቤቶችን ጨምሮ ወልድያ ከተማ ህንጻ ሹም ገምቶ በላከው ብር 2,140,033.42 /ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ ሽህ ሰላሳ ሶስት ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ የጨረታው ማስታወቂያ ከሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምሌ 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ  በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ጨረታው ሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00  እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ /መግዛት/ የሚፈልጉ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መግዛት /መጫረት/ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሽናፊው እንደታወቀ ከንብረቱ ዋጋ ውስጥ 25 በመቶ /ሀያ አምስት /በመቶ ለሐራጅ ባይ እንዲያስረክብ እና ጠቅላላ ዋጋውን በ15 ቀን ውስጥ ከፍሎ አጠቃሎ መጨረስ ያለበት መሆኑን ታውቆ በተወሰነው ጊዜ የንብረቱን ዋጋ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወጭው ተቀንሶ ቀሪ ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 422 ፣423 ፣425 እና 426 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ገቢ እንደሚሆን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here