የአፈ/ከሳሽ አቶ ይርጋ ከፋለ እና የአፈ/ተከሳሽ ዶ/ር መላኩ የኔነህ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርከር ጉዳይ በፍ/ሰላም ከተማ 02 ቀበሌ አዋሳኙ በምሥራቅ መንገድ፣ ምዕራብ አማረ ጌቴ፣ በሰሜን ደብሬ ደሳለው እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል ተወስኖ የሚገኘውን ቤት በመነሻ ዋጋ 602,579 (ስድስት መቶ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር)በጨረታ ይሸጣል። ስለሆነም ፍርድቤቱ መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ንብረቱ በሚገኝበት ቀበሌ /ቦታ/ ላይ በግልጽ ጨረታ አጫርቶ የሚሸጥ መሆኑን አስታውቋል። በዚሁ መሰረት ከየካቲት 17/2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 17/2017 ዓ.ም የሚቆይ እና መጋቢት 18/2017 ዓ.ም ጨረታው የሚካሄድ በመሆኑ በተጠቀሰው ሰዓት፣ ቀንና ቦታ ላይ በመገኘት ማንኛውም ግለሰብ ቀርቦ መጫረትና መግዛት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የፍ/ሰላም ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት