በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት አንደኛ ዙር የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያና ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለአሸናፊዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ከ14/12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ 300.00 (ሦስት መቶ ብር)፣ ለሆቴል 400.00 (አራት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ሲፒኦ 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ14/12/2016 እስከ 27/12/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ27/12/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለምትፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ28/12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ግቢ ከንቲባ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በስ.ቁ 058 775 17 75 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 76 ማግኘት ይቻላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት