የመሬት ሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
10

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሬት ባንኪንግና ፋይናንሲንግ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ መሠረት ለመኖሪያ እና ድርጅት አገልግሎት የተዘጋጀ ቦታዎችን 1ኛ ዙር በግልጽ መደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከቀን ጥቅምት 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ለመኖሪያ እና ለድርጅት በመክፈል ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት ዘወትር በስራ ስዓት ሰነድ መግዛት እና መወዳደር ይችላል፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ እና መሸጫ ጊዜ ከጥቅምት 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ይሆናል፡፡
  2. ጨረታው የሚዘጋው ጫረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት ተቆጥረው በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሁሉም የጨረታ አስፈፃሚ ቡድን አባላት እና አግባብ ያለው አካል የሚሰይማቸውን ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
  3. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ዝግ ከተደረገበት ቀን በኋላ ባለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገው ምድር አዳራሽ ይሆናል፡፡
  5. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች እና ቢሮ ቁጥር 05 ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 07 72 /058 221 00 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here