የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ 53 እና ለድርጅት 5 በድምሩ 58 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ በኋላ ከጥቅምት 24/2018 እስከ ህዳር 05/2018 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ወጥቶ ይውላል፡፡ ስለዚህ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም አካል የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከጥቅምት 24/2018 እስከ ህዳር 05/2018 ዓ/ም ድረስ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 07 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ህዳር 05/2018 ዓ/ም በ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ህዳር 06/2018 ዓ/ም 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፣ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ለድርጅት 15 በመቶ እና ለመኖሪያ 20 በመቶ የተከፈለበት እንዲሁም ኦርጅናል (ዋናውን) ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው ፡፡
- የጨረታ ቦታዎችን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በተለጠፈው ሳይት ኘላን መመልከት በአካል መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

