የመሬት ሊዝ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

በደቡብ ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት  ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር  ቡድን በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አግባብ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ አንድ  መሰረት ለ10ኛ ዙር ጨረታ የንግድ 4 እና የመኖሪያ  2 ቦታዎችን ለተጫራቾች በጨረታ ዉድድር ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ህጋዊ ግለሰብ አክሲዩን፣ ድርጅት ወይም ማህበር እንዲሁም ማንኛዉም ህጋዊ ተጫረቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ጨረታው መጫረት የሚፈልጉ ግለሰብ፣ ማህበር፣ አክሲዩን ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት  ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 210 እየመጡ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታዉ የሚቆየዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ10ኛዉ ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያዉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ሆኖ ለመጫረት የፈለጉትን የጨረታ ቦታ ዋጋ በካሬ ሜትር በአሀዝና በፊደል በመግለጽ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታዉ የሚከፈትበት 11ኛዉ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንድሁም ካላንደር የሚዘጋ ሆኖ ከተገኘ በ10ኛዉ ቀን 11፡30 ታሽጎ ዝግ የሆነዉን ቀን አልፎ በሚገኘዉ የስራ ቀናት 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የሚሆን የሞሉትን ቦታ የመነሻ ዋጋ በካ/ሜ ተባዝቶ የሚያገኘዉ ዋጋ 30 በመቶ እና በላይ  በዝግ ሂሳብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን ጨረታዉ ተከፍቶ አሸናፋ ከተለየ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዳዉኑ ከሚቀጥለዉ የስራ ቀናት ጀምሮ ተመላሽ  የሚሆን ሲሆን ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያሸነፉበት ቦታ ቅድሚያ የሊዝ ክፍያ እስከሚከፍሉ የማይመለስ ይሆናል፡፡
  6. ተሸናፊ ተጫራቾች ለሲፒኦ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ጨረታ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ መዉሰድ አለባቸዉ፡፡ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ የማይወስድ ከሆነ በሲፒኦ የተያዘዉ ገንዘብ የማይመለስ ሆኖ ለከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ ይደረጋል፡
  7. የጨረታ አሸናፊዉ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ በ10 የስራ ቀናት ዉስጥ የሊዝ ቅድመ ክፍያዉን ማለትም ከጠቅላላ ክፍያዉ 40 በመቶ በመክፈል ዉለታ መፈጸም አለበት፡፡
  8. ለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ ዉስጥ የጨረታ ህጉን ተከትሎ የሚጠለፍ ማስታወቂያዎችና በስልክ ቁጥሮቻችን 033 220 00 33 ወይም 033 220 10 73 /09 84 15 53 97/ ደዉለዉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. መ/ቤቱ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here