በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት የከተማ መሬት ል/አስ/ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም የመኖሪያና የሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ፡-
- ከ13/09/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/፣ ለሆቴል 400.00 /አራት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ሲፒኦ ሃያ አምስት በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ13/09/2016 ዓ.ም እስከ 27/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ27/09/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለምትፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ28/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ግቢ ከንቲባ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በስ.ቁ /058-775-1775 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 76 ማግኘት ይቻላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡