በደ/ጎንደር ዞን ከተማ እና መሰረተ ልማት መምሪያ በሰዴ ሙጃ ወረዳ ከተማ እና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት የአዳዳ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት መሬት ልማት ማናጅመንት ዋና የስራ ሂደት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ 721/2004 መሰረት በ2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረት ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ሶስት ቦታዎች ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል አንድ ቦታ ሲሆን ግንባታ የሚገነቡ G+0 የቅይጥ አገልግሎት የሚውል ቦታ ዲዛይን V sheape ሲሆን የንግድ አገልግሎት የሚውለው ቦታ L sheape ለጨረታ የሚቀርቡ መሆናቸውን እየገለፅን፡፡
በአጠቃላይ አራት ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ሰው ወይም ድርጅት ከ27/08/2017 ዓ.ም እስከ 08/09/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት አስር የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ አዳዳ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ 400 ብር በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማስገቢያ ቀን ከ27/08/2017 ዓ.ም እስከ 08/09/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት አስር የመንግስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በንዑስ ማዘጋጃ ቢሮ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ08/09/2017 ዓ.ም በ 10 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ08/09/2017 ዓ.ም በ11 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳዳ ከተማ ንዑስ ማዘገጃ ቤት ግቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ቦታዎችን በአካል ለመጎብኘት ከፈለጉ በ08/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ድረስ በመገኘት ከጨሬታ ኮሚቴው ጋራ መጎብኘት ይችላሉ ወይም በማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ በተለጠፈው ፕላን መመልከት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በሚል በበኩር ጋዜጣ በአየር ላይ እንዲውልልን ስንል እንጠይቃለን፡፡
የአዳዳ ከተማ ንዕስ ማዘጋጃ ቤት