የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
130

የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2016 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ 50 እና ለድርጅት 2 አገልግሎት በድምሩ 52 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ መጫረት የምትፈልጉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ጨረታው በአየር ላይ ከሰኔ 3/2016 እስከ ሰኔ 14/2016 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡መጫረት የሚፈልጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች  የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ / በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ከሰኔ 03 / 2016 እስከ 14/10/2016 ዓ/ም ድረስ ባሉት 10 የስራ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 02 ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው ሰኔ 14 /2016 ዓ/ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 15/2016 ዓ/ም በ 3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
  5. ሁሉም ተጫራቾች በፖስታ አሽገው ማስገባት ያለባቸው ፤የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፣በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ለድርጅት 15በመቶ እና ለመኖሪያ 20በመቶ የተከፈለበት ዋናውን /ኦርጅናል/ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ናቸው፡፡
  6. የጨረታ ቦታዎችን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በተለጠፈው ኘላን መመልከት እና በአካል መጎብኘት ይቻላል፡፡
  7. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here