የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
173

የእብናት ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ለአብናት ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤጽ የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት 4ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት የመሬት 02 G+4 የመሬት ሊዝ በግልፅ ጨረታ አውጥቶ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በእብ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  3. የጨረታው ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ስም በማሠራት የተሠራውን (ሲፒኦ) እና ሰነድ የተገዛበትን የ300.00 /የሦስት መቶ ብር/ ደረሰኝ ሁለቱን በአንድ ላይ በማድረግ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ከኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅርብ አለበት፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ ገቢ አድርጎ ኦርጅናል ሰነዱን የእ/ከ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ማስገባት አለበት፡፡
  6. ጨረታው ተጫሪቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋይናን ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ 4፡40 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. የቦታዎች የሊዝ መነሻ ዋጋ ለካሬ ለድርጅት 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ነው፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ አስራ አምስት በመቶ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሽናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  10. የግንባታ ደረጃ የድርጅት (G+4) ነው፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የቦታው አገልግሎት እያዳንዱ ምድብ ከሰንጠረዡ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
  13. በአጭር ጌዜ ውስጥ ወደ ግንባታ የሚገባና የሚያጠናቅቅ መሆን አለበት፡፡
  14. ለጨረታ የወጣው የቦታ ብዛት ለድርጅት 02 ነው፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእብናት ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here