የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
98

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2017 የበጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት ለ2ኛ ዙር የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያ፣ ለሆቴልና ለገበያ ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
1. ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ከጥር 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ 300.00 ብር፣ለሆቴልና የገበያ ማዕከል 400.00 ብር የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ሲፒኦ 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡.
2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ01/05/2017 ዓ.ም ዓ/ም ጀምሮ እስከ 14/05/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
3. ጨረታው የሚዘጋው በ14/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
4. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጽ መርሀ-ግብር መሰረት ይሆናል፡፡
5. ጨረታው የሚከፈተው በ15/05/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስ.ቁ 058-775-1775 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here