የደብረ ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለመኖሪያ 45 እና ለድርጅት3 አገልግሎት በድምሩ 48 ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር ትችላላችሁ።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ከ15/07/2017 እስከ 26/07/2017 ዓ/ም ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት እና በመመዝገብ የማይመለስ ብር00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከ15/07/2017 እስከ 26/07/2017 ዓ/ም ድረስ ባሉት 10 የስራ ቀናት በመንግስት የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 02 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ26/07/2017 ዓ/ም በ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው 27/07/2017 ዓ/ም በ 3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ
ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
ሁሉም ተጫራቾች በፖስታ አሽገው ማስገባት ያለባቸው።
- የሀሳብና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ።
- በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ለድርጅት 15በመቶ እና ለመኖሪያ 20በመቶ የተከፈለበት።
- ኦርጅናል / ዋናውን/ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ናቸው፡፡
- የጨረታ ቦታዎችን በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በተለጠፈው ኘላን መመልከትና በአካል መጎብኘት ይቻላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደብረ ታቦር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ