የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
107

የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ል/ጽ/ቤት የመሬት ባንኪንግና ፋይናንሲንግ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ መሰረት ለመኖሪያና ለድርጅት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን 2ኛ ዙር በግልጽ መደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ከመጋቢት 22/2017 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር ለመኖሪያና ለድርጅት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት ሰነድ መግዛት እና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ እና መሸጫ ጊዜ 22/07/2017 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 2:30 እስከ 11፡00 ይሆናል፡፡
2. ጨረታው የሚዘጋው የሥራ ቀናት ተቆጥረው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሁሉም የጨረታ አስፈፃሚ ቡድን አባላት እና አግባብ ያለው አካል የሚሰይማቸውን ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል፡፡
3. ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ዝግ ከተደረገበት ቀን በኋላ ባለው የመጀመሪያ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገው ምድር አዳራሽ ይሆናል፡፡
5. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በዳንግላ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቦታዎች በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች እና ቢሮ ቁጥር 6 ወይም በስልክ ቁጥር 058 221 07 72 ወይም 058 221 00 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረት ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here