የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
65

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት የ4ኛ ሩብ አመት ለ3ኛ ዙር ለመኖሪያ ፣ለሆቴልና ለገበያ ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ ከግንቦት 18/2017 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/  ፣ለሆቴልና የገበያ ማዕከል ብር 400 /አራት መቶ ብር/  የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ18/09/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 03/10/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. ጨረታው የሚዘጋው በ03/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚከፈተው በ04/10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  4. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በስ.ቁ 058 775 17 75 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here