የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
13

በምዕራብ ጎጃም ዞን የፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት ለ2ኛ ጊዜ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት የመኖሪያ 30 ቦታዎችን እና ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ 5 በድምሩ 35 የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. ከየካቲት 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ መኖሪያ 300 ብር፣ለሆቴል 400 ብር የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ሲፒኦ 35 በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር ጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከየካቲት 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 17/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓትብቻ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በየካቲት 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው በየካቲት 18/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  5. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በስ.ቁ 058 775 08 13 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 76 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here