በደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ አንድ መሰረት ለ11ኛ ዙር ጨረታ ለንግድ 2 እና የመኖሪያ ቦታዎችን ለተጫራቾች በጨረታ ውድድር ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- መጫረት የሚፈልግ ግለሰብ ፣ማህበር አክሲዩን ወይም ድርጅት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 210 እየመጡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆየዉ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ10ኛዉ ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይክፈታል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሆኖ ለመጫረት የፈለጉትን የጨረታ ቦታ ዋጋ በካሬ ሜትር በአሀዝና በፊደል በመግለጽ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛዉ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በአል ሆኖ ከተገኘ በ10ኛዉ ቀን 11፡30 ታሽጎ ዝግ የሆነዉን ቀን አልፎ በሚገኘዉ የስራ ቀናት 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ ) የሞሉትን ቦታ የመነሻ ዋጋ በካ.ሜ ተባዝቶ የሚገኘው ዋጋ 20 በመቶ እና በላይ በዝግ ሂሳብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን ጨረታዉ ተከፍቶ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያዉኑ ከሚቀጥለዉ የስራ ቀናት ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን ሲሆን ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያሸነፉበት ቦታ ቅድሚያ የሊዝ ክፍያ እስከሚከፍሉ የማይመለስ ይሆናል፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለሲፒኦ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ጨረታው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ መዉሰድ አለባቸዉ፡፡ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ የማይወስዱ ከሆነ በሲፒኦ የተያዘዉ ገንዘብ የማይመለስ ሆኖ ለከተማ አስተዳደሩ የፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ ይደረጋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ በ10 የስራ ቀናት ዉስጥ የሊዝ ቅድመ ክፍያዉን ማለትም ከጠቅላሳ ክፍያዉ 25 በመቶ በመክፈል ዉለታ መፈጸም አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ ዉስጥ የጨረታ ህጉን ተከትሎ በሚለጠፉ ማስታወቂያዎችና በስልክ ቁጥሮቻችን 033 220 00 33 ወይም 033 220 10 73 /09 84 15 53 97 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

