የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለአብናት ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር በጨረታ የድርጅት 01 G+2 እና 01 G+1 የመኖሪያ 05 G+0 የመሬት ሊዝ በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በእብ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያበቀው በ10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋዉን በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት የተሰራዉን (ሲፒኦ) ሰነድ የተገዛበትን ብር 300 ደረሰኝ ሁለቱን በአንድ ላይ በማድረግ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ከኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅርብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ ገቢ አድርጎ ኦርጅናል ሰነዱን የእ/ከ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫሪቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ 4፡40 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የቦታዎች የሊዝ መነሻ ዋጋ ለካሬ ለድርጅት ብር 500 ለሌሎቹ ቦታዎች ግን ብር 200 ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ለድርጅት 15 በመቶ ለመኖሪያ 20 በመቶ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ የድርጅት 01 G+2 እና 01 G+1 ሌሎቹ ደግሞ G+0 ነዉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የቦታው አገልግሎት ለእያንዳንዱ ምድብ ከሰንጠረዡ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
- በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ግንባታ የሚገባና የሚያጠናቅቅ መሆን አለበት፡፡
- ለጨረታ የወጣው የቦታ ብዛት ድርጅት 02 መኖሪያ 05 ነዉ፡፡
- ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ገ/ፅ/ቤት በመምጣት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

