የመሬት  የሊዝ   ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ

0
10

የእብናት ከተማ አስ/ገ/ጽ/ቤት ለአብናት ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በተደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት 3ኛ ዙር በጨረታ የድርጅት 01 G+4፣ 01 G+2 እና 01 G+1  የመኖሪያ ደግሞ 08 G+0 የመሬት ሊዝ በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በእብ/ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30  ብቻ ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታው ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያበቀው  በ10ኛው ቀን እስከ  11፡30  ብቻ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋዉን በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት የተሰራዉን (ሲፒኦ) ሰነድ የተገዛበትን የ300 ብር ደረሰኝ ሁለቱን በአንድ ላይ በማድረግ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት  ከኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅርብ አለበት፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ ገቢ አድርጎ ኦርጅናል ሰነዱን በእ/ከ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ  በ11ኛዉ ቀን ማስገባት አለበት፡፡
  6. ጨረታው ተጫሪቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋይናን ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ጨረታው በወጣ በ11ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ታሽጎ 4፡40  ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. የቦታዎች የሊዝ መነሻ  ዋጋ  ለካሬ – ለድርጅት  ብር 500  ለሌሎቹ  ቦታዎች ግን ብር 200  ነው፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ለድርጅት 15 በመቶ ለመኖሪያ 20 በመቶ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  10. የግንባታ ደረጃ የድርጅት  01 G+4 ፡ 01 G+2 እና 01 G+1 ሌሎቹ ደግሞ G+0   ነዉ፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የቦታው አገልግሎት ለእያንዳንዱ ምድብ ከሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
  13. በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ግንባታ የሚገባና የሚያጠናቅቅ መሆን አለበት፡፡
  14. ለጨረታ የወጣው የቦታ ብዛት ድርጅት 03 መኖሪያ 08 ነዉ፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ገ/ጽ/ቤት በመምጣት አገልግሎቱን  ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእብናት ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here