ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቀበሌ 2 ሎት 1. ከትምህርት ጽ/ቤት እሰከ ዳኘ ተፈራ ቤት መጨረሻ እና ሎት 2 ከዳኘ
ተፈራ ቤት መጨረሻ እስከ ገበያ ማዕከል ለሚሠራው የጠጠር መንገድ እና የካናል ግንባታ ሥራ በግልፅ ጨረታ በሎት (በጥትል) አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን
መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገልጻለን፡-
1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2015 ዓ.ም የሥራ ግብር ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ያጠናቀቀ እና የታደስ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
2. ጨረታ ማስክበሪያ አንድ በመቶ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ ቀድሞ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች ያሸነፉትን የጠጠር መንገድ እና የካናል ግንባታ ሥራ የሞሉትን ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ ወድያውኑ በማስያዝ ውል በመውስድ የተጠየቀውን የጠጠር መንገድ እና የካናል ግንባታ
ሥራ የጥራት ደረጃ ጠብቆ ሊሠራ ይገባል፡፡
4. ሥራውን ለመሥራት የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ደረጃ 7 እና በላይ የሆኑ ተቋራጮች ሆነው በቂ እውቀት ልምድና ሙያ ያላቸው በዘርፉ በሕጋዊ መንገድ የተሰማሩ መሆን እለባቸው፡፡
5. ያሸነፉትን የጠጠር መንገድ እና ካናል ግንባታ ሥራ ውል የማይወስዱ ወይም ውል ከወሰዱ በኋላ የጠጠር መንገድ እና የካናል ግንባታ ሥራ በጥራት ሰርቶ የማያስረክብ ተጫራች ቢያጋጥም
መሥሪያ ቤቱ ለውል ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ መውረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ አንድ ዓመት ለሚደረስ ጊዜ በጨረታ እንዳይሳተፉ የማገድ ስልጣኑን ለመጠቀም ይገደዳል፡፡
6. ማንኛም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን የማይመለስ አንድ ኮፒ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ አንድ ኮፒ እና ቫት የምስክር ወረቀት የማይመለስ አንድ ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት
ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ለሚሠራው የጠጠር መንገድ እና የካናል ግንባታ ሥራ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ታስቦ በ 22 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ መካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ
ቁጥር 210 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡
9. ጨረታው በዚሁ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የዓል
ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
10.ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 210 መግዛት ይችላል፡፡
11.አሸናፊው ተወዳዳሪ ወይም ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ካሠሪው መሥሪያ ቤት ጋር በፍትህ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
12.መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
13.ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኙት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 220 10 24 ወይም 09 14 45 28 92 ደውሉ ማግኙት ይችላሉ፡፡
የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት