የፍሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ዋንዛ፣ የሀበሻ ጽድ እና ዋራካ ዛፎች በስተቀር ቁጥር የተሰጣቸው 210 ዛፎች ማለትም ባሕር ዛፍ፣ አርዘሊባኖስ፣ ሰሳ እና ሌሎች ዛፎችን በሎት ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሕጋዊ የአጣና ፈቃድ ያላቸው ገዥዎች በታሸገ ፖስታ በጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚገዙበትን ጥቅል ዋጋ በመሙላት የመጫረቻ ሳጥን ላይ እንዲአስገቡ ይጋበዛሉ፡፡
1. ተጫራቾች አግባብ ያለው በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሥራ ፈቃዳቸው የአሳደሱበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የዛፍ ሽያጭ መነሻ ዋጋ 800,000.00 (ስምንት መቶ ሽህ ብር) ነው፡፡
3. የግብር ክፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፋ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዱቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አምስት በመቶ በሲፒኦ ወይም በሞ/ል 85 ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡ አሸናፊው ዛፉን ሲቆርጥ በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ቢያደርስ ወጭውን እራሱ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
5. የሽያጭ ጨረታ ማወዳዳሪያ ሃሣብ ይህ ጨረታ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ የሚውል ይሆናል፡፡
6. ጨረታው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ ከፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አያስተጓጓልም፡፡
7. የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 775 10 16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል