ልዩ የዓይን ጠብታዎች ማንበቢያ መነፀር ከመጠቀም እና ቀዶ ህክምና ከማድረግ በተሻለ በእርጅና ምክንያት የደከመ የማየት ችሎታን እንደሚያሻሽሉ ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡
እድሜ እየገፋ ሲሄድ የሰዎች በቅርበት ያሉ እንደ ጽሁፍ የመሰሉትን ለመለየት ይቸገራሉ፤ በዚህም መነፀር ለመጠቀም እና ቀዶ ህክምናን አማራጭ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ በተለየ በ766 ኛው በአውሮፓ የዓይን ሞራ ግርዶሽ 43ኛው ጉባኤ ላይ በ766 ታካሚዎች ላይ በተደረገ ጥናት የዓይን ጠብታን በየእለቱ መገልገል እይታን እንደሚያሻሽል ነው በውጤቱ የተመላከተው፡፡
“ፒሎካርፒን” እና “ዲክሎፍኖክን” የተሰኙ የዓይን ጠብታዎችን አከታትለው የወሰዱ ከ55 ዓመት በላይ የሆናቸው 766 ናሙና ጥናት ተሳታፊዎች ሲሆኑ በጥቂት ቀናት መሻሻል ማሳየታቸው ተረጋግጧል፡፡
በጥናቱ ከጥቂት ቀናት እስከ 12 ወራት በተደረገ ክትትል የዓይን ግፊት መጨመር፣ ብዥታ የመሳሰሉት ቀንሰው መስታዋላቸውን ተገንዝበዋል- አጥኚዎቹ፡፡
በጥናቱ ወቅት ጠብታዎች የሚወስዱ ታካሚዎች ሦስት ነጥብ ሰባት በመቶ መበሳጨት፣ ሦስት ነጥብ ስምንት በመቶ ራስ ምታት የመሳሰሉ መለስተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳጋጠሟቸው አጥኚዎቹ ለይተዋል፡፡ ከገሚኘው ውጤት አንፃር ግን ከዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን ነው ያሰመሩበት – ተመራማሪዎቹ፡፡
ለእይታ ችግሮች የሚወሰዱ ማጉያ መነፅር መቀጠም እና ቀዶ ህክምና ማድረግ ለሁሉም የችግሩ ተጠቂዎች ለማድረስ ከውጪ አንፃር ከባድ ከመሆኑ ባሻገር ለተጠቃሚዎቹ የማይመቹ መሆናቸው ነው የተገለፀው በአጥኚዎቹ፡፡
የታካሚዎቹ የእይታ መሻሻል እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል ያስገነዘቡት ተመራማሪዎቹ ከዚያን ጊዜ በኋላም የሚወሰዱትን ጠብታዎች በማስቀጠል እይታቸውን ማሻሻል እንደሚችሉ ነው በማደማደሚያነት ያስነበቡት – ድረ ገፆች::
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም