የሥራ ሰዓት መቆጣጠሪያን በጭምብል

0
61

በቻይና ዢጂያን ግዛት ዌንዙ ከተማ በመንግሥት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ጐረቤታማቾች፣ በፊት ገፅ መለያ የስራ ሰዓት መቆጣጣሪያ መሣሪያን ስራ ላይ ያልተገኙን ምስል በያዘ /Noaa NOAA-National Oceanic and Atnospheric Adminstration/ በጭምብል እንደተገኙ በማስመሳል ሲያጭበረብሩ ተጠርጥረው መያዛቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ  ለንባብ አብቅቶታል፡፡

የቻይና ሚዲያዎች በቅርቡ ይፋ አንዳደረጉት፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በተደረገባቸው ክትትል ባልደረቦቻቸው በስራ ገበታቸው ላይ ባልተገኙበት በስራ ሰዓት መቆጣጠሪያው እንደተገኙ ተመዝግበው መገኘታቸው ተረጋግጧል፡፡

በስራ ሰዓት ላለመገኘት አጭበርብረዋል በሚል ተጠርጥረው የተያዙትን ሲመራ የነበረ ግለሰብ መያዙን ያስነበበው ድረ ገጹ አንድ ወይም ሁለት ሰራተኞች የብዙዎቹን ምስል በያዘ የወረቀት ጭምብል ያሉ  አስመስለው መመዝገባቸው ነው የተደረሰበት፡፡

ከስራ የቀሩት ግን በሌላ ቦታ የግል ስራቸውን ሲያከናውኑ እንደነበርም ነው ድረ ገጹ ያስነበበው፡፡

በጭምብል በማጭበርበር ምንያህል ሰራተኞች ከስራ እንዳቀሩ በውል ባይታወቅም ከፊት ገፅ የሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን ከፍ ብሎ በሚገኝ የደህንነት መከታተያ የምስል መቅረጫ ካሜራ ምስላቸው ተቀርፆ መገኘቱ ነው ለንባብ የበቃው፡፡

በማጭበርበር ተጠርጥረው የተያዙቱ ከስራ እንዲቀሩ ከረዷቸው የመንግስት ሰራተኞች  አበል ወይም ክፍያ የሚቀበሉ መሆናቸው እንደተደረሰበት ነው የተብራራው – በድረ ገጹ፡፡

በመጨረሻም ቴክኖሎጂ በረቀቀበት ዘመን ተጠርጣሪዎቹ በወረቀት በተሰራ ጭምብል እንዴት ማሽኑን ሊያጭበረብሩ ቻሉ? የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የታህሣስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here