የሥያሜ ለውጥ

0
186

መጋቢት 19 ቀን 1922 ዓ.ም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የቱርክ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ‘አንጎራ’ ሥሟ ተለውጦ አንካራ ስትባል፤ የአገሪቱ አንደኛ ከተማ እና በሮማ ቄሳር ቁስጥንጢንያ ወይም ኮንስታንቲኖፕል (Constantinople) ሥሟን ቀይራ ኢስታንቡል ተባለች።

ይህ ለውጥ የመጣው የኦቶማን ቱርክ መንግሥት አንደኛው የዓለም ጦርነት ከተሸነፈ እና በሃይል ይዟቸው የነበሩትን መሬቶች ከለቀቀ በኋላ ነው።

በዚህም ሥርዎ መንግሥቱ ይዟቸው የነበሩትን ግሪክ፣ ፈረንሳይ እና ሌሎች ሃገራት መሬት ተነጥቋል። ብዙም ሳይቆይ አገዛዙ ከሥልጣን ተወግዷል።

ምንጭ፦ ኒው ወርልድ ኢንሳይክሎፒዲያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here