ሚያዚያ 8 ቀን 1965 ዓ.ም የአስር ሺ እና አምስት ሺ ርቀቶች ንጉሥ ኢትዮጵያው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በአርሲ፣ አሰላ ከተማ ተወለደ። የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የይቻላል እና የፅናት ምልክት የሆነው ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገብረ ሥላሴ አልበገሬነቱን በዓለም መድረኮች ሁሉ ያሳዬ ድንቅ አትሌት ነው።
ከሌላ ዓለም የመጣ ፍጡር እስከማለት የሚዲያ ሰዎች ለብቃቱ ቃላት የሚያጡለት ኃይሌ በ10ሺ ሜትር ለረጅም ጊዜ የቆየ የሪከርድ ባለቤት ነበር።
በአምስት ሺህ እና በ10ሺህ ኃይሌ ካለ ሁሌም ወርቅ አለ። በርካታ የወርቅ ሜዳሊያዎችን በተለያዩ የኦሎምፒክ ውድድሮች በማሸነፍ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በተደጋጋሚ ከፍ አድርጓል። ኢትዮጵያ ሁሌም ስትዘክረው የሚኖር የምንግዜም ጀግናዋ ነው፣ እንኳን ተወለድክ ኃይሌ።