የራሱን የገዛዉ

0
72

ተሽከርካሪውን ካቆመበት ስፍራ የተሰረቀው ባለንብረት ከመድን ድርጀት በተሰጠው ገንዘብ የጠፋችበትን የራሱን ተሽከርካሪ ሳያውቅ መልሶ መግዛቱን ዩፒ አይ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት አስነብቧል፡፡

የ36 ዓመቱ እንግሊዚያዊ የኮምፒውተር ባለሙያ ኢዋን ቫለንታይን ጥቁር ሆንዳ ተሽከርካሪውን ካቆመበት መንገድ ዳር ይሰረቃል፡፡ ፈጥኖ በአቅራቢያ ላለ  የፓሊስ  ጣቢያ ቢያመላክትም የማግኘት እድሉ ዝቅተኛ  መሆኑ ይነገረዋል፡፡

 

ኢዋን ፓሊስ የሰጠውን አስተያየት ይዞ ለኢንሹራን ኩባንያ ያመላክታል፤ የኢንሹራንስ ኩባንያውም ሁኔታውን አጣርቶ ክፍያውን ይፈፅማል፡፡ ኢዋንቫ ላንታይን ገንዘቡን ተቀብሎ ከጠፋችበት ተሽከርካሪ ጋር ተመሳሳይነት ያላትን አፈላልጐ ይገዛል፡፡

ኢዋን ቫላንታይን ከመድን ኩባንያ በተሰጠው 26 ሺህ ዶላር የገዛትን የተሰረቀችበትን ተሽከርካሪ ምትክ በቅርበት ሲመረምር (ውስጥ እና ውጪዋን) ሲመለከት የራሱን መኪና መልሶ ሳይገዛ እንዳልቀረ ይጠረጥራል፡፡ የገዛት ተሽከርካሪ ቀለም፣ የተመረተችበት እና ያገለገለችበት ዓመትም ከጠፋችበት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

 

በፍተሻው በውስጥ የተለጣጠፉ ጌጦች መጫጫራቸውን፤ የጭስ መውጫው መጥቆሩን ተመልክቶ በጠፋችበት መትክ የሸጠለት ጋራዥ የተሰረቀ መሆኑን እያወቀ እንደሸጠለት ለማመን ይቸገራል፡፡

ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ፓሊስ እና የሆንዳ ተሽከርካሪ ጋራዥ ባለቤትም ተሰረቀች በተባለችው እና በምትክ በተገዛችው መካከል ልዩነት ማግኘት ይቸገራሉ፡፡

 

በሁኔታው ግራ የተጋባው ፓሊስም የተገዛችውን ተሽከርካሪ ለኢንሹራንስ ኩባንያው ያስረክባል፡፡

ኢዋን ቫላንታይን በተሽከርካሪዋ ወጪ እና ውስጣዊ የላይኛው ኮፈን የተለጣጠፉ ምስሎች፣ የመደገፊያ ሽፋን መላላጥ እንጂ ተመሳሳይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

 

በመጨረሻም ተሽከርካሪዋ አዲስ ታርጋ ቢለጠፍባትም የጉዞ አሰሳ መመዝገቢያው ሲፈተሽ የራሱ የኢዋን ቫላንታይን እና የቤተሰቡ አድራሻ በመገኘቱ የራሱን ተሽከርካሪ መልሶ መግዛቱ ተረጋግጧል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here