የሲል አሸናፊነት

0
25

በአሜሪካ የዋሽንግተን ግዛት ፓስፊክ ውቅያኖስን በሚዋሰንበት ቀጣና በዓሳ ነባሪዎች ከበባ ውስጥ የገባ የባህር አንበሳ “ሲል” ሁነቱን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎችን ወደ ያዘች ጀልባ ዘሎ በመግባት ከአዳኞቹ ማምለጡን ዩፒአይ ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት አስነብቧል::

ቀጣናውን በጀልባ በመዘዋወር ሁነቶችን በመቅረጽ ሲዝናኑ የነበሩ ጓደኛማቾች በሦስት መቶ ሜትር ያህል ርቀት ገዳዮቹ ዓሳነባሪዎች የባህር አንበሳውን  “ሲል” ከበባ ውስጥ ሲያስገቡት መመልከት ችለዋል::

ከተመልካቾቹ አንዱ ዓሳ ነባሪዎቹ ከበው ለማጥቃት ልምምድ የሚያደርጉ ይመስሉ እንደነበር ታዳኙም ካባህሩ ሽቅብ እየዘለለ ለማምለጥ በደመነፍስ ሲፍጨረጨር ማስተዋሉን አካፍሏል- በድረ ገጹ::

በመዝናናት ላይ የነበሩት ጓደኞማቾች የጀልባዋን ሞተር አጥፍተው ሁነቱን መከታተላቸውን ይቀጥላሉ፤ የአዳኞች እና የታዳኙ ትርኢትም እንዲሁ::

የዓሳ ነባሪዎቹ ከበባ እና የባህር አንበሳው የማምለጥ ጥረት ቀጥሎ ሳለ አዳኞቹ እና ታዳኙ ወደ ጀልባዋ እንዲቀርቡ የጀልባዋን ሞተር አጥፍተው መጠባበቃቸውን ይቀጥላሉ:: ከሰላሳ ደቂቃ በኋላም የባህር ዓንበሳው ዘሎ ጀልባዋ ላይ ይወጣል::

የባህር ዓንበሳው ጀልባዋ ላይ ዘሎ መውጣቱን የተመለከቱት ዓሳ ነባሪዎቹ ጀልባዋን ይከቧታል:: ዓሳ ነባሪዎቹ ጀልባዋ ላይ  ካሉ ታዳኙ እና ተመልካቾቹ ጓደኛሞች ጋር አስራ አምስት ደቂቃ ያህል ተፋጠው ተስፋ ቆርጠው ቀጣናውን ለቀው  ይበተናሉ::

ቡድኑም የጀልባዋን ሞተር አስነስቶ በባህርም ሆነ በየብስም መኖር የሚችለውን “ተሳፋሪ” እንደያዘ ወደ ባህር ዳርቻ ማምራቱን ድረ ገጹ  አስነብቧል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሕዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here