የስጋ ስርቆትን ለመከላከል

0
172

በአውስትራሊያ የሚገኘው “ድሬክስ” በሚል ስያሜ የሚታወቀው ሱፐር ማርኬት መገኛ አመላካች መሣሪያ /ጂፒኤስ/ በስጋ ማሸጊያዎች ላይ በማኖር ስርቆትን ለመከላከል መቻሉን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በደቡብ አውስትራሊያ የሚገኘው የታሸገ ስጋ መሸጫ ሱፐር ማርኬት በስርቆት ከፍ ላለ የገንዘብ ኪሳራ ሲዳረግ ቆይቷል። በተለያዩ ከተሞች ሱፐር ማርኬቱ  ካሉት 67 ቅርንጫፎች በዓመት እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የታሸገ ስጋ ይሰረቃል፡፡

በአውስትራሊያ በተለያዩ ውድ የሽያጭ ቁሳቁስ መሸጫ መደብሮች በተመሳሳይ የቦታ ማመላከቻ መሣሪያ ስርቆትን ለመከላከል እንደሚገለገሉ ተጠቅሷል፡፡ የታሸገ ስጋ ስርቆትን ለመከላከል አድራሻ አመለካች መሣሪያ በመጠቀም ግን ድሬክስ ሱፐር ማርኬት የመጀመሪያ መሆኑ ነው በድረ ገፁ የተገለፀው፡፡

የስጋ ማሸጊያዎቹ ጂፒኤስ የተገጠመላቸው 35 ዶላር የሚያወጡት፤ የስጋ መሸጫ ዋጋው ከ50 እስከ 100 ዶላር መሆኑን የተናገረው የሱፐር ማርኬቱ ኃላፊ ጆንፐል ድሬክ እየተሞከረ ያለው መከላከያ አዋጪ መሆኑን ነው ያሰመረበት፡፡

ሱፐር ማርኬቱ ስርቆት መከላከያ ስልቱን ለ13 ሳምንታት መሞከሩን እና በሁሉም ሱፐር ማርኬቶች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ውሳኔ ላይ መድረሱ ን ነው ያረጋገጠው፡፡

የስርቆት መከላከያ ስልቱ በወጪ አዋጪ መሆኑንም በማጠቃለያነት አስምሮበታል፤የሱፐር ማርኬቱ ኃላፊ፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here