የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

0
270

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ ለሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 4. ህትመት፣ ሎት 5. የመኪና
መለዋወጫ እና ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን
እንገልፃለን፡፡
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ወይም (ቲን) ያላቸው፡፡
3. የግዥ መጠን ከ200,000.00(ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ 50.00 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመግዛት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ
ወረዳ በሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ስዓት በፊት ማስገባት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባችሁ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሁለት በታሸገ ኢንቨሎት ፖስታ በጥንቃቄ ተሞልቶ በሆስፒታሉ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን
ውስጥ ከ03/05/2016 ዓ.ም እስከ 20/05/2016 ዓ.ም ድረስ ለከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ20/05/2016 በ2፡00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸግና በቀን 21/05/2016 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ
ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 2፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ዕለት ህዛባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ስዓት
ይከፈታል፡፡
9. አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 የሥራ ቀናት የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውሉን መፈፀም ይኖርበታል፡፡ በተባለው ቀን
ቀርቦ ውሉን የማይፈፅም ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይሆንና ለሁለተኛው አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ተገቢውን
የጨረታ ማስከበሪያና አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስረከቢያ ማስያዝ አስባቸው፡፡
10.የጨረታው አሸናፊ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በማምጣት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ እቃው ገቢ የሚሆነው በባለሙያ እየታየ ትክክል
መሆኑንና መሥራቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
11.ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ስስ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥ 09 18 21 27 03 / 09 18 41 90 47 መደወል
መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
13.ተቀባይነት የሌላቸው ተመላሽ የሚሆኑ እቃዎች ትራንስፖርት እና ሌሎች ወጭ በአቅራቢው በራሱ የሚሸፍን መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚያቀርቡት ዶክሜንት ጥራቱን የጠበቀ፣ ስርዝ
ድልዝ የሌለውና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
14.በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ሕጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡
ማሳሰቢያ፡-አሽናፊ የሚለየው በሎት ወይም በድምር ነው::

የሻሁራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here