የቀይ ባሕር አካባቢን የጂኦ – ፖለቲካ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የቀጣናው ሀገራት ትብብር ወሳኝ ነው ተባለ

0
69

የቀይ ባሕር አካባቢን የጂኦ – ፖለቲካ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የቀጣናው ሀገራት ትብብር ወሳኝ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ተናግረዋል። 3ኛው የቀይ ባሕር ቀጣናዊ ጂኦ – ፖለቲካ ፎረም “የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ቀጣና ሀገራት ለኢኮኖሚያዊ፣ ለደኅንነት ትብብር እንዲሁም መልካም አጋጣሚዎች፣ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

ኢዜአ እንደዘገበው በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የሥራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ምሁራንና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የቀይ ባሕር አካባቢን የጂኦ – ፖለቲካ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የቀጣናው ሀገራት ትብብር ወሳኝ ሚና አለው።

ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በትብብር እየሠራች መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕርን ደኅንነት ከማስጠበቅ አኳያ የባሕር ላይ ዝርፊያዎችን ጨምሮ ሌሎች ሕገ – ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የሚኖራት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በኲር የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here