የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል

0
161

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል አድራሻ ባሕር ዳር አባይ ማዶ ቀበሌ ሕዳር 11 ከኮበል ኢንዱስትሪ ጎን ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎችን ሎት 1.
ጫማዎች፣ ሎት 2. የተዘጋጁ ልብሶች፣ ሎት 3. የብስክሌት መለዋወጫ፣ ሎት 4. ብረታ ብረት፣ ሎት 5. ፈርኒቸር፣ ሎት 6. የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት 7. የደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ፣
ሎት 8. የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 10. የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 11. ሴፍቲ ሹዝ እና ሎት 12. የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት
ይፈልጋል፡፡
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት /ቲን/ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
3. ተጫራቾች የዋጋውን ጠቅላላ አንድ በመቶ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ዋጋቸው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
5. ማዕከሉ ከሚገዛዉ ዕቃ የዋጋውን ሃያ በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው፡፡
6. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስረከቢያ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሞላት አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 60.00 /ስልሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
10. የእቃዎችን አይነት /ሞዴል/ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን በ3፡30 ታሽጎ ወዲያዉ በ4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው
ባሉበት ይከፈታል፤ ቀኑ ቅዳሜ ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
12. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
13. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም የሚወረስ
ይሆናል፡፡
14. ማዕከሉ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ለማንኛውን ግዥ ለዕቃዎች ከ10,000.00 (ከአስር ሽህ ብር) በላይ እና ለአገልግሎት ከ3,000.00 (ከሦስት ሽህ ብር) በላይ ሁለት በመቶ የቅድመ ግብር ተቀንሶ ይቀራል፡፡
16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 321 54 82 /058 820 97 84 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here