ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2016 ዓ.ም የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነዱን
የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን
ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የቴክኒካል ማወዳደሪያ ሰነድ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በተለያየ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unConditional Bank Garanty/
ከኦርጅናል ወይም ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች
ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ግ/ንብ/አስ/ንዑ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡30
ይከፈታል፡፡
9. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ
በማስያዝ እና ውል በመፈፀም ባሕርዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት በመቅረብ ወደ ሥራ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 320 50 79 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት