የታዳጊዎችን እድገት የሚገድበዉ

0
23

የዓየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው የሙቀት መጨመር በታዳጊ ልጆች አካላዊ እና አእምራዊ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ማሳረፉን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በአሜሪካ የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ቡድን መሪ ረዳት ኘሮፌሰር ጆርጅ ኩዋርታስ ከስድስት ሀገራት የተመረጡ ተሳታፊዎች በመጠየቅ የሰጡትን መልስ ለተደረሰበት ድምዳሜ በግብአትነት መገልገላቸውን አስርድተዋል፡፡

ቡድኑ የተሰበሰበውን መረጃ ለመተንተን እና ውጤቱን ለመቀመር የታዳጊዎችን የእድገት መለኪያ /early childhood development Inde /ECDI/ ከማንበብ፣ ቁጥሮችን ከመለየት እና ማገናዘብ ክሂሎትን ከአካላዊ እድገት ጋር አጣምሮ የመገምገም ተግባርን ከውኗል፡፡ በዚሁ ከ2017- እስከ 2020 እ.አ.አ በተወሰደው መረጃ ትምህርት፣ ጤና፣ የተመጣጠነ መግብ አወሳሰድ እና የግል ጤና አጠባበቅ (ሳኒቴሽን)ን አጣምረው መተንተናቸው ነው የተገለፀው- በጥናቱ፡፡

የቡድኑ ጥናት እና ምርምር ሞቃት የዓየር ሁኔታ በታዳጊዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር ውጤቱ በግልጽ አመላክቷል፡፡ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እንቅልፍ መንሳት፣ በአንጐል ውስጥ እብጠትን ሊያስከትል እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ እነዚህ ለውጦች የማስታወስ ችሎታን፣ ስሜትን እና የታዳጊዎችን የማገናዘብ አቅም የሚደግፉ የአንጐል ክፍሎችን ሊነኩ ወይም ለያውኩ እንደሚችሉ ነው የደረሱበት ተመራማሪዎቹ፡፡

በማደማደሚያነት የሙቀት መጨመር ከአመጋገብ ስርዓት፣ ከእውቀት ወይም የማገናዘብ (ኮግኒቲቭ)እድገት ከስሜት መረጋጋት እና የበሽታ የመከላከል አቅም ወዘተ ጋር እንደሚገናኝ ነው የተሰመረበት::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የታህሣስ 13  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here