የአሜሪካ አብዮት

0
206

 የህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

አሜሪካ አሁን ያለበትን ግዛት እስክትይዝ ድረስ ከተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች የሰዎች ሶስት የስደት ማእበሎች ተስተናግደዋል። እኛም በመጀመሪያው ክፍል ወደ አሜሪካ የፈለሱ የመጀመሪያ ሰፋሪዎችን ለማየት ሞክረናል ቀጣዩን እነሆ።

የመጀመሪያ ተወላጅ አሜሪካውያን አዴኒያንስ ይባላሉ። የአሁኗን አሜሪካ መሰረት ጣይ በመሆን በ600 ቅ.ዓ አካባቢ የጭቃ መቃብር ቦታዎችን እና ምሽጎችን በመስራት ጀምረዋል። ይሁን እንጂ አዴኒያንስ በተለያዩ ቡድኖች የመዋጥ ወይም የመፈናቀል ፈተናዎችን ተጋፈጡ። በተለይ የወል ስማቸው ሆፕዌሊያንስ በሚባሉ ልዩ ልዩ ቡድኖች ተውጠዋል ወይም ተፈናቅለዋል። በደቡባዊው ኦሃዮ ዋነኛ የባህላቸው ማእከል መገኘቱን የሚጠቁሙት የታሪክ መረጃዎች ሆፕዌሊያኖች በመቶዎቹ ኪሎ ሜትሮችን የሚያካልሉ ነጋዴዎች እንደነበሩ ይታመናል።

ሆፕዌሊያኖች በ500 ዓ.ም አካባቢ እነርሱም ጠፍተዋል። የጠፉትም ቀስ በቀስ አንድ ሰፊ የነገዶች ቡድን በወል ስሙ ሚሲሲፒያውያን የሚባሉትን ተክተው ነበር። በኢሊኖይስ ግዛት፣ ኮሊንስቪል አጠገብ ያለ ካሆይስክ የተሰኘ  አንድ ከተማ በ12ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ 20ሺ ያህል ሰዎች እንደነበሩ ይታሰባል። በአሁኑ የደቡብ ምእራብ አሜሪካ ውስጥ አናሳዚ የተባሉት የሆፕ ሕንዳውያን አባቶች በ900 ዓ.ም አካባቢ የገነቡት እስከ 800 ክፍሎች ያሉት የድንጋይ ቤተመንግሥት በኮሎራዶ ግዛት ላይ ተገኝቷል።

እግራቸው የሰሜን አሜሪካን አፈር የረገጡ የመጀመሪያ አውሮፓውያን ኖርስ(Norse) የሚባሉ ሕዝቦች ስለመሆናቸው ተጨባጭ መረጃ አለ። የኖርስ ሕዝብ፣  ቀዩ ኤሪክ በ977 ዓ.ም አካባቢ አንዳች የሰፈራ መንደር ወደ መሰረተበት ከግሪንላንድ ወደ ምእራብ አቅጣጫ ተጉዘው ነበር። በ993 ዓ.ም ላይ ደግሞ ልጁ ለይፍ የዛሬዋን ካናዳ ሰሜን-ምስራቅ ጠረፍ አስሶ እንዳገኘ እና አንድ ክረምት በዚያው እንዳሳለፈ ይታሰባል።

ክርስቶፈር ኮሎምቦስ ለእስያ ምእራባዊ መስመር ፍለጋ ተጉዞ በካሪቢያን መልህቁን ካሰረ ከአምስት ዓመታት በኋላ በ1489 ዓ.ም ቬኔሽያዊው መርከበኛ ጆን ካቦት በአንድ የብሪታኒያው ንጉሥ ተልእኮ ኒውፋውንድላንድ ውስጥ ደረሰ። ካቦት ወዲያው ቢረሳም፣ ቆይቶ ግን ብሪታኒያ ሰሜን አሜሪካን የማግኘት ፍላጎት መሰረት ሆኗል።

በሰሜን አሜሪካ እንግሊዝ 13 የሰፈራ እና የእርሻ ልማት ቅኝ ግዛቶችን መስርታለች፤ ከ16ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ  እነዚህ ቅኝ ግዛቶችም በኋላ ላይ የኃያሏ አሜሪካ ግዛት የሆነውን፣ ከሰሜን በኩል ከካናዳ ጀምሮ በደቡብ እስከ ፍሎሪዳ ያለውን ስፍራ እና ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ዳር መሬት እስከ አፓላቻን ተራሮች ይደርሳል:: ከአፖላቻን ተራሮች ማዶ ግን ጥቂት የነጮች ሰፈራዎች ነበሩ:: በእነዚህ ግዛቶች የሕዝቡ ቁጥር በፍጥነት አደገ፤ ለዚህ ምክንያቱ ቅኝ ገዥዎቹ ገና ወጣት ሆነው ስለሚያገቡ እና ብዙ ልጆች ስለሚወልዱ ነበር:: እንዲሁም ከአውሮፓ የሚደረገው ፍልሰት ህዝቡን እንዲጨምር አድርጎታል:: ስደተኞች በአብዛኛው የሚመጡት የተሻለ ሕይወትን ፍለጋ ነበር:: በመሆኑም በ1767 ዓ.ም የ13ቱ ቅኝ ግዛቶች የሕዝብ ቁጥር ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ደርሶ ነበር::

በ13ቱ ቅኝ ግዛቶች ሕዝብ በሙሉ ሁሉም የአውሮፓዊ መነሻ የነበራቸው አይደሉም:: ነገር ግን አሜርኢንዲያንስ የተባሉት ተወላጅ አሜሪካውያን የሚገኙበት ሲሆን ቁጥራቸው በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች በእጅጉ ቀንሷል:: በሽታ ብዙዎችን ቀጥፏል፤ እንዲሁም በየጊዜው ከአውሮፖ የፈለሱ ሰፈራዎች ብልጫ ባለው ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ከትውልድ ቀያቸው አፈናቅለዋቸው እስካሁንም ትውልዱ እየመነመነ ይገኛል:: ከአሜሪኢንዲያንስ በተጨማሪ፣ በ1767 ዓ.ም በ13ቱም ቅኝ ግዛቶች ከአፍሪካ የመጡ ግማሽ ሚሊዮን ያክል ጥቁሮች ነበሩ:: እነዚህ  የአትላንቲክ ውቅያኖስን አቋራጭ በነበረው የባሪያ ንግድ በኩል የመጡ ናቸው::

እነዚህ 13ቱ ቅኝ ግዛቶች ባሮች የነበሯቸው ሲሆን ነገር ግን አብዛኞቹ ባሮች በደቡባዊው  የእርሻ ጣቢያ ቅኝ ግዛቶች ውስጥ ነበር:: በነፃነት ጦርነቱ ወቅት ወይም ወዲያው ካለቀ በኋላ ባርነት በሰሜኑ ግዛቶች ሲያከትምለት በደቡቡ ግን ቀጥሎ ነበር:: በመሆኑ የቅኝ ግዛቱ ዘመን በአስራ ሦስቱ ግዛቶች ውስጥ ኢኮኖሚው በፍጥነት ሰፍቷል::

ምክንያቱም ወደ አውሮፓ የትምባሆና ሩዝ፣ ዲንዲጎ፣ ጥራጥሬ እና ሌሎች ምርቶችን መላኳ እና የህዝብ ቁጥሩ ማደግ በዋናነት እንደምክንያት ይጠቀሳሉ:: የኢኮኖሚዎቹ መስፋት ቢኖርም ቅሉ በ13ቱም ቅኝ ግዛቶች ውስጥ ኢኮኖሚያዊ እኩልነት አለመኖር በተያያዙ የመደብ ልዩነቶች ነበር::

አሥራ ሦሶቱም ግዛቶች በእንግሊዝ መንግሥት እና በቅኝ ግዛቶቹ ላይ ሕግ ማውጣት በሚችሉት በእንግሊዝ ፓርላማ ስልጣን ሥር ነበሩ:: እነዚህ ሕጐች  ንግዱን እና የቅኝ ግዛት ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠሩ ነበሩ:: ሕጎቹ የቅኝ ግዛት ኢኮኖሚው እንግሊዝን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ የተዘጋጁ ነበሩ:: ሆኖም እስከ 1463 ዓ.ም ድረስ ሕጎቹ በደንብ ያልተተገበሩ እና በቅኝ ተገዥዎች ላይ ብዙ ችግር ያላስከተሉ ነበሩ::

በእንግሊዝ አገዛዝ ስር የበሩት 13ቱም ግዛቶች፣ ከፍተኛ የራስ ገዝነት ስልጣን ነበራቸው፡ እያንዳንዱ ቅኝ ግዛት በእንግሊዝ መንግሥት የተሾመለት አስተዳዳሪ አለው:: ነገር ግን እያንዳንዱ ቅኝ ግዛት የተመረጠ ምክር ቤት (asscmbry) አለው:: እነዚህ ምክር ቤቶት ግብር ለአካባቢ ተግባር እንዲውል ድምፅ መስጠት እና ሕግ የማፅደቅ ሚና ነበራቸው:: ሆኖም በ18ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ የቅኝ ግዛቶች ዘንድ “አሜሪካዊያን” ጎን የሚል ስሜት እየጀመረ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥሮ የነበረበት እና ይህ ስሜትም ከ1755 ዓ.ም ወዲህ ከእንግሊዝ ጋር የተፈጠረ ግጭት በማደጉ ምክንያት ጨምሯል:: በዚህ መካከል የእንግሊዝ መንግሥት በቅኝ ግዛቶቹ ላይ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር የማድረግ ውሳኔ አሳለፈ:: ይህ ደግሞ ከቅኝ ግዛቶቹ ጋር ይበልጥ እያፈራረቀው ሄደ:: ቅኝ ተገዥዎቹ ለእንግሊዝ ፖሊሲ ያላቸውን ጥላቻ በተለያዩ መንገዶች አሳዮ:: እንደ ጀምስ ኦቲስ፣ ፓትሪክ ሄነሪ አና ሳሙኤል አዳምስ የተባሉ አርበኛ መሪዎች በንግግሮቻቸው እና በድርጊት የሕዝቡን ፀረ እንግሊዝ ስሜት ከፍ አደረጉት:: አንዳንድ አመፆችም ሲፈነዱ ታየ:: በ1765 ዓ.ም ላይ የቦስተን ዜጐች ሕንዳውያን መስለው በቦስተን ወደብ ላይ የእንግሊዝ የሻይ ቅጠል መርከቦችን ግብር እንዲከፍሉ ያገቱበት ተግባር አንዱ ነበር:: የአሜሪካ ነጋዴዎችም የእንግሊዝን እቃዎች ላለመግዛት ተስማሙ:: ይህ የአሜሪካውያኑ የእንግሊዝ አዲስ መርሃ ግብርን ልዩ ልዩ እርምጃዎች በመቃወም የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ለአንዳች አዲስ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ስርዓት ያላቸውን ፅኑ አቋም ያሳይ ነበር:: ነግር ግን የእንግሊዝ ምላሽ ለቅኝ ግዛቶች አዲስ ሕጎችን በማፅደቅ መገደብ እና መቅጣት ብቻ ሆነ::

ይህ ደግሞ ለወታደራዊ ትግል ያነሳሳ ተግባር በመሆን ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ በመሆን አዲስ ነፃ ማህበረ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር ለመመስረት ትግሉን አፋፋሙት። የትጥቅ ትግሉን እንዲመራ ኮሎኔል ጆርጅ ዋሽንግተንን በመሾም ግዛቶቹ ለነፃነት የትጥቅ ትግሉን በማካሄድ ለውጤት አብቅተዋል። ቶማስ ጃፈርሰን አስራ ሶስቱ ቅኝ ግዛቶች (ኒው ሃምፕሻየር፣ ማሳቹሴትስ፣ ኮነቲከት፣ ሮድ አይላንድ፣ ኒው ዮርክ፣ ኒው ጀርሲ፣ ፔንስልቬንያ፣ ዴላዌር፣ ሜሪላንድ፣ ቨርጂኒያ፣ ሰሜን ካሮላይና፣ ደቡብ ካሮላይና እና ጆርጂያ) በእንግሊዞች ያም ሆኖ ግን ለአብዛኞቹ ነፃ ሰዎች ምርጫ ክፍት የሆኑ የአካባቢ መንግስታት ነበሯቸው። እጅግ በጣም ከፍተኛ በሆነ የወሊድ መጠን፣ ዝቅተኛ የሞት መጠን እና የተረጋጋ ሰፈራ፣ የቅኝ ገዥው ህዝብ በፍጥነት አደገ፣ የአሜሪካ ተወላጆችን ሸፈነ። የ1730ዎቹ እና 1740ዎቹ የክርስቲያን ተሀድሶ እንቅስቃሴ ታላቁ መነቃቃት በመባል የሚታወቀው በሃይማኖት እና በሃይማኖታዊ ነፃነት ላይ ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል።

በሰባት አመታት ጦርነት (1756–1763) በአሜሪካ የፈረንሳይ እና የህንድ ጦርነት በመባል በሚታወቀው የብሪታንያ ሃይሎች ካናዳን ከፈረንሳይ ያዙ። የኩቤክ ግዛት ሲፈጠር፣ የካናዳ የፍራንኮፎን ህዝብ ከኖቫ ስኮሺያ፣ ኒውፋውንድላንድ እና አስራ ሶስት ቅኝ ግዛቶች እንግሊዝኛ ተናጋሪ የቅኝ ግዛት ጥገኝነት ተነጥሎ ይቆያል። እዚያ ይኖሩ የነበሩትን የአሜሪካ ተወላጆችን ሳይጨምር፣ አስራ ሶስት ቅኝ ግዛቶች በ1770 ዓ.ም ከ2.1 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ነበራቸው፣ ይህም ከብሪታንያ አንድ ሶስተኛው ያህል ነበር። ቅኝ ግዛቶቹ ከብሪታንያ ርቀው ራስን በራስ የማስተዳደር እድገት አስችሏቸዋል። ነገር ግን ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ስኬት የብሪታንያ ነገሥታት በየጊዜው የንጉሣዊ ሥልጣኑን እንደገና ለማስከበር እንዲሞክሩ አነሳስቷቸዋል።

ነፃነት

በአስራ ሦስት ቅኝ ግዛቶች ከብሪቲሽ ኢምፓየር ጋር የተዋጋው የአሜሪካ አብዮታዊ ጦርነት አውሮፓዊ ያልሆነ አካል በዘመናዊ ታሪክ ከአውሮፓ ሃይል ጋር የፈፀመው የመጀመሪያው የተሳካ የነጻነት ጦርነት ነው። አሜሪካውያን የ”ሪፐብሊካኒዝም” ርዕዮተ ዓለም አዳብረዋል፣ መንግሥት በሕዝብ ፍላጎት ላይ ያረፈ መሆኑን በአካባቢያቸው የሕግ አውጭ አካላት ላይ አሳልፈው ነበር። “እንደ እንግሊዛዊ መብታቸውን” እና “ያለ ውክልና ግብር አይከፈልም” ሲሉ ጠይቀዋል። እንግሊዞች ግዛቱን በፓርላማ እንዲያስተዳድሩ አጥብቀው ጠየቁ፣ ግጭቱም ወደ ጦርነት ተለወጠ። ሁለተኛው ኮንቲኔንታል ኮንግረስ፣ የተባበሩት ቅኝ ግዛቶችን የሚወክል ጉባኤ፣ የነጻነት መግለጫን ሐምሌ 4 ቀን 1776 ዓ.ም በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። ይህ ቀን በየዓመቱ የነፃነት ቀን ተብሎ ይከበራል።

የመረጃ ምንጭ፡-በሪፍ ሂሰትሪ ኦፍ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ

(መሠረት ቸኮል)

በኲር የህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here