በአርበኝነት ይፋለሙትና መቀመጫያ
መቆሚያ ያሳጡት የጦር አዝማቾች ራስ
ደስታ ዳምጠው እና ደጃዝማች በየነ መርዕድ
በጀግንነት የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊትን
በዝዋይ አካባቢ ሲፋለሙ ህይወታቸውን
የገበሩት በዚህ በያዝነው ሳምንት የካቲት 16
ቀን 1929 ዓ.ም ነበር።
በግራዚያኒ የሚመራው የፋሽስቱ ጦር
ከእነዚህ ጀግኖች የጦር መሪዎች አርበኞች
ጋር ሲፋለም የማታ ማታ ድል ቀናው።
ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች
ሕይወታቸውን የሰውት በዚህ ዕለት ነበር።
ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ
በጥይት ደበደቧቸው፡፡ እነርሱ ሞተው
ህይወት ለእኛ የሰጡንን ጀግኖቻችን እንዲህ
ሞተውም ሲዘከሩ ይኖራሉ።