ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግ/ጨ/መ/ቢ/ቁ/02/2ዐ16
የአብክመ መሬት ቢሮ ካልም ፕሮጀክት በመደበኛ እና መደበኛ ካፒታል በጀት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎችን፣ የፈርኒቸር እቃዎችን፣
የህትመት ሥራ አገልግሎት ግዥ፣ የኤሌክትሪክ እና የመስክ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. የጨረታውን ሠነድ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋምቢ ቲቺንግ ሆስፒታል አጠገብ ከሚገኘው መሬት ቢሮ
ቁጥር 18 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሠረት ሞልተው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው
እስከሚዘጋበት እስከ 3፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ክፍሉ በሚያዘጋጀው የመክፈቻ ቦታ ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን
16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /bid security/ ለፈርኒቸር እቃዎች 5,000.00 (አምስት ሽህ ብር)፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 400,000.00 (አራት መቶ ሽህ ብር)፣ ለመስክ
እቃዎች 5,000.00 (አምስት ሽህ ብር )፣ ለጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር)፣ ለኤሌክትሪክ እቃዎች 15,000.00 (አስራ አምስት ሽህ ብር)
እና ለህትመት ሥራ አገልግሎት ግዥ 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ከታወቁ ባንኮች በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ
በማሠራት ከዋጋ መሙያ ቅጹ ጋር በማያያዝ እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ከመስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የግዥመጠናቸው 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ላሉ እቃዎች ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡
፡ የቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑ ድርጅቶች በድርጅታቸው ስም የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ በማድረግ አሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
8. ከ20,000.00 (ከሃያ ሽህ ብር) በላይ ላሉ ግዥዎች 7.5 በመቶ ቫቱን ቢሮው ቀንሶ የሚያስቀር ይሆናል፡፡
9. አሸናፊው የሚለየው ዝቅተኛ የመገምገሚያ መስፈርቱን አሟልተው ከተገኙት ድርጅቶች ውስጥ በእያንዳንዱ እቃ በፋይናንስ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ መሬት ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058
220 71 31 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአብክመ መሬት ቢሮ