የአንቲቫይረስ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ሕዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቃስ በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ሕዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው:: ማህበሩ ለዳታ ሴንተር ሰርቨር እና ለ150 ኮምፒውተሮች አገልግሎት የሚውል አንቲቫይረስ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልፅ ጨረታ ለሦስት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል:: ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው::
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ ሆኖ ዋና እና ቅጅ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው::
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መሥሪያ ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል:: በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል::
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ )

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here