የአንደኛ ደረጃ የሐራጅ ማስታወቂያ

0
18

የአፈ/ካሳሽ እነ ወ/ሮ ባንች አምላክ ገነቱ (5 )ሰዎች እና በአፈ/ተከሳሽ  ወ/ሮ ብርቄ ታከለ ጣልቃ ገብ ወጣት ያብስራ ገነቱ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር ክስ ጉዳይ የማዕከላዊ ጐንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት፤ የአፈ/ተከሳሽ እንደፍርዱ ሊፈጽሙ ባለመቻላቸው ምክንያት በጐንደር ከተማ በዞብል ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 ቀጠና 02 የሚገኝ የካርታ ቁጥር 2408/75 የቦታ ስፋት 300 ካሬ ሜትር በአዋሳኝ በምስራቅ፣ በሰሜን እና በምዕራብ መንገድ እንዲሁም በደቡብ ቁጥር 05 የሚያዋስነው ቤትና ቦታ መነሻ ዋጋ 3,523,338.82 (ሶስት ሚሊየን አምስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰማንያ ሁለት ሳንቲም) በሆነ መነሻ ዋጋ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ በአንደኛ ደረጃ የሐራጅ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡ በመሆኑም ከላይ በአዋሳኝ የተጠቀሰውን ቤት እና ቦታ መጫረት ወይም መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጥር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ቤቱ ከሚገኝበት ቦታ ድረስ በመቅረብ ቤትና ቦታውን አይቶ መጫረት እና መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንድታሟሉ እንገልጻለን፡፡

  1. ተወዳዳሪዎች ከጠዋቱ 3፡00 እሰከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ቤቱን እና ቦታን አይቶ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ገዥ ሲያሸንፍ አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ያስዛል፡፡
  3. ገዥ ሲያሸንፍ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃሎ ከከፈለ ስመንብረቱ ወዲያውኑ እንዲዛወርለት

ይደረጋል፡፡

  1. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በጨረታ ወቅት መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታ የሚወዳደሩ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪላቸው ይሆናል፡፡
  3. በጨረታ ወቅት ሁከት የሚፈጥር በህግ ይጠየቃል፡፡
  4. ስመ ንብረት ማዛወሪያ በጨረታ አሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  5. ጨረታው በማዕከላዊ ጐንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐራጅ ባይ የሚመራ ይሆናል፡፡
  6. ከላይ በዝርዝር የቀረበውን የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ አሟልታችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ቤቱ ከሚገኝበት በጐንደር ከተማ ዞብል ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 ቀጠና 02 ድረስ በመገኘት ቤቱንና ቦታውን በአካል ቀርበው በማየት በጨረታው ቀንእና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here