የእርጅናን መርቻው

0
204

በቻይና ቾንጊንግ ነዋሪ የሆኑት የ70 ዓመቱ አዛውንት ላለፉት 45 ዓታት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራታቸው እርጅናን ረተው ጤናማ፣ ጠንካራና ፈርጣማ አካል ማጐልበታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል፡፡

ዞው ሂፒንግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሥራት የጀመሩት በ1979 እ.አ.አ ነው፡፡ ያኔ ዞው እጃቸው በገባ መጽሄት ላይ መሮጥ የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በማንበባቸው ነበር የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን የጀመሩት፡፡ የያኔው ጐልማሳ በመኖሪያ አካባቢያቸው አቅራቢያ በሚገኝ ተራራ ከግርጌው እስከ እናቱ ሁለት  ሺህ 500 ደረጃዎችን /እርከኖችን/ ይሮጣሉ፡፡ በተራራው ላይ ለመውጫ መውረጃ የተሰሩ እርከኖችን እየዘለሉ ወጥተው ይወርዳሉ። ይህም የእጅና የእግር ጡንቻዎቻቸውን አጠንክሮላቸዋል፡፡

ዞው ሂፒንግ ያላሰለሰ በዕለት ተዕለት የሚሰሩት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካላቸውን እያደሰ ከእድሜያቸው አጋማሽ ላይ የሚገኙ አስመስሏቸዋል፡፡

ዞው ሂፒንግ ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያገኙትን ጠቀሜታ “ሕይወት በሩጫ ውስጥ ናት፤ በጣም አስፈላጊው ነገር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመሥራት የአካል ጥንካሬን መጠበቅና የተስተካከለ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ነው” ሲሉ ወጣቶችን ያነሳሳሉ፣ ይመክራሉ፡፡

ዞው ሂፒንግ በየዕለቱ የአየር ንብረቱ ሞቃትም ይሁን ቀዝቃዛ ያለ ጫማ ባዶ እግራቸው ነው የሚሮጡት፡፡ ከ40 ዓመታት በፊት ተለክፈውበት የነበረውን አጉል ሱስ ማጨስ እና አልኮል መጐንጨትን ርግፍ አደርገው መተዋቸውን ለሌሎች በአርአያነት አካፍለዋል፡፡

“ዕድሜ ቁጥር ብቻ ነው” የሚሉት አዛውንቱ ለዚህ ያበቃቸው ምን እንደሆነ ለሚጠይቋቸው ሁሉ “ህይወት በእንቅስቃሴ ውስጥ ናት፡፡ ጤናማ የአኗኗር ስልት ሁልጊዜ ወጣት እንድትሆን ያስችላል” ሲሉ ይመክራሉ በመጨረሻም የማይቋረጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እርጅናን መግቻ ቁልፍ መሆኑን በመግለጽ ነው ከልምድ ያገኙትን እውነት በማጋራት ያደማደሙት፡፡

 

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here