የእቃ አቅርቦት እና የእጅ ዋጋ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
141

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የቢሮ እድሳት የፍኒሽንግ ዕቃዎች ሎት 1. እና የእጅ ዋጋ ሎት 2. አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ ፡፡

በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ሕጋዊ  የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

የግዥው መጠን ከ200.000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

የቢሮ እድሳት የፍኒሽንግ ዕቃዎች ሎት 1. እና የእጅ ዋጋ ሎት 2. አገልግሎት ግዥ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ (ANRS Plan and Development Bureau) በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡

ማንኛውም ተጫራች የቢሮ እድሳት የፍኒሽንግ እቃዎች ሎት 1. እና የእጅ ዋጋ ሎት 2. በጥንቃቄ በመለየት በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 03 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001  ሕዳር 03  ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡

አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡

መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here