የእናት ውለታዋ

0
114

በቱርክ ኢስታንቡል ከተማ አሳዳሪ አልባዋ አራስ ውሻ በጠና ታሞ የደከመ ቡችላዋን እንስሳት ህክምና መስጫ ክሊኒክ በር ላይ ማድረሷን ኦዲቲ ሴትራል ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አበቅቶታል፡፡

በቱርክ ኢስታንቡል ግዛት፣ ቤይል ክድዙ በተሰኘ መንደር ጥር 5/2017 የእንስሳት ወዳጆች መንገድ ላይ ያገኙትን ቡችላ ወደ እንስሳት ህክምና ተቋም ማምጣታቸውን የእንስሳት ሀኪሙ ተናግረዋል፡፡ ሀኪሙ የተጣለ ነው የተባለውን ብቸኛ ቡችላ ለማከም በመጣደፍ ላይ ሳሉ ግን በሩ ላይ ሌላ የደከመ ቡችላ በአፏ ያንጠለጠለች ውሻ ይመለከታሉ፡፡  ከአፏ መሬት ላይ ያሰቀመጠችው ቡችላ የሞተ ቢመስለውም ፈጥኖ መርምሮ በቅዝቃዜ ተጐድቶ የልብ ምቱ የደከመ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ዶ/ር ባቱራአፕ ኦግሀን ሁለቱንም የተጐዱ ቡችላዎች ህይወታቸውን ለመታደግ ጥረት ማድረጋቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ለተሰኘ የፈረንሳይ የዜና ማስራጫ አስረድቷል፡፡

የእንስሳት ህክምና ተቋሙ ሀኪም ዶ/ር ባቱራአፕ እና የህክምና ቡድን አባላቱ ያልተለመደውን የእናት ውሻዋን እና የቡችሎችዋን ሁነት በማህበራዊ ድረ ገፆች አጋርተዋል፡፡ በርካታዎቹም አስገራሚውን አጋጣሚ እናት ለልጅ የምትከፍለው በሁሉም የውሻ ዝርያዎች ያለ  ማረጋገጫ መሆኑን ነው ያሰመሩበት፡፡

ዶ/ር ባቱራአፕ ኦልሀን ከቡድን አባሎቻቸው ጋር ባደረጉት ርብርብ ሌሎች  አገልግሎቶችን  አቁመው እናት ውሻዋ እና ሁለቱ ቡችሎቿ ባደረጉላቸው እንክብካቤ በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘታቸውን አብስረዋል፡፡

በመጨረሻም እናት ውሻዋ እና ቡችሎችዋ ቶሎ እንዲያገግሙ ለማስቻል ተጨማሪ ወተት እንድትጠጣ መመቻቸቱም ነው የተገለፀው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here