የእፅዋት ተፈጥሯዊ መከላከያን ለመድሃኒት

0
3

ተመራማሪዎች እፅዋት ተፈጥሯዊ መከላከያ የሚገነቡበትን ሂደት በመኮረጅ በቤተ ሙከራ የተሻሻሉ መድሃኒቶችን በፍጥነት፣ በዝቅተኛ ዋጋ እና አካባቢን በማይጐዳ መልኩ ለማምረት ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ላይ መሆናቸውን ሳይቴክ ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡

እፅዋት በተፈጥሯዊ መከላከያነት “አልካሎይድ” የሚባሉ ኬሚካሎችን ነው የሚያመርቱት፡፡ ይህንን ስልት በመኮረጅም ተመራማሪዎች በኬሚካል በቤተ ሙከራ የተሻሻሉ አዳዲስ መድሃኒትን በአጭር ጊዜ፣ በአነሰ ዋጋ፣ ተፈጥሮን በማይጐዳ መልኩ ለማምረት መቃረባቸውን የዮርክ ዩኒቨርሲቲ በመረጃ ምንጭነት ይፋ አድርጓል፡፡

በዮርክ ዩኒቨርሲቲ የስነ ህይወት ትምህርት ክፍል ተመራማሪውዶክተር ቤንጃሚን ሊችማን   እፅዋት እና ረቂቅ ነፍሳት (ባክቴሪያ) የተለያዩ ተፈጥሯዊ ኬሚካሎችን እንደሚያመርቱ ጠቁመዋል፡፡

እፅዋትን ለመከላከያነት የሚያውሉት ሰዎች ለማስታገሻ እና ለመድሃኒትነት የሚገለገሉበትን ከእፅዋቱ ሰብስቦ በፋብሪካ ከማምረት ይልቅ ተኪን በቤተሙከራ ማምረት ቀላል እና ተመራጭ መሆኑን ነው ያሰመሩበት ተመራማሪዎቹ፡፡

ዶክተር ቤንጃሚን ሊችማን አዲሱ ስልት ጠቃሚ ኬሚካል ውህዶችን በቤተሙከራ ማዘጋጀት እንደሚያስችል ገልፀው ብርቅዬ እፅዋትን በመሰብሰብ ላይ የሚኖረውን  ጥገኝነት፣ የጊዜ እና የሀብት ውድመት ይቀንሳል ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም “አልካሎይድ” ተፈጥሯዊ የእፅዋት መከላከያ መርዛማ ሊሆን ስለሚችል በመድሃኒትነት ቀምሞ አገልግሎት ላይ ለማዋል ከፍተኛ ቁጥጥር እና ጥንቃቄ  ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here