የኦሞ ታችኛዉ ሸለቆ

0
100

የኦሞ የታችኛው ሸለቆ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ነው የሚገኘው:: ሸለቆው 165 ኪሎ ሜትር ርዝመት ተለክቷል:: ሸለቆው ከቱርካና ሐይቅ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች የሚርቅ ሲሆን በዓለም በቅድመ ታሪክ ቅሪት መገኛነቱም ከፍ ያለ እውቅና አግኝቷል::

በሸለቆው ቀጣና ከተገኙ በርካታ ጥንታዊ ቅሪት አካላት በተለይም ሆሞግራሲሊስ በሰው ልጅ ቅድመ ታሪክ ዝግመተ ለውጥ (ኢቮሉሽን) ጥናት በአራት እግር ከመጓዝ ወደ ሁለት እግር የተደረገው ሽግግር ማረጋገጫ ቦታ ሆኗል::

በታችኛው የኦሞ ሸለቆ ውስጥ ለዘመናት የተነባበረው የደለል ክምችት የሰው ልጅ ያለፈባቸው መሰረታዊ የዝግመተ ለውጥ  “ምእራፎች” አሻራ መገኛም ሆኗል:: በዚህም ቀጣናው የኮንሶ ፌጀጅ (የፓሊዮንቶሎጂ) ሳይንሳዊ የምርምር  መዳረሻን አጠቃሎ ይዟል::

በኦሞ ሸለቆ የተገኙ ጥነታዊ ቅሪቶች  ከአንድ እስከ ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዬን ዓመታት እንደሚዘልቁ የባዮስትራቲግራፊ፣ ራዲዮ ሜትሪክ እና ማግኔቶ ስትራቲግራፊካል መለኪያ ሚዛኖች አረጋግጠዋል::

በኦሞ ሸለቆ ቀጣና ውሰጥ ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመው ሳይንሳዊ የምርምር ጣቢያ ከየ አህጉራት እና አገራት ለሚሰበሰቡ በመስኩ የላቀ እውቀት ላላቸው ተመራማሪዎችም መዳረሻ ሆኗል::

የጥንታዊ ቅሪት ተመራማሪዎቹም በሸለቆ ወደተለያዩ ቀጣናዎች በመዘዋወር ባደረጓቸው ፍለጋዎች ሉሲን መሰል የቀደምት የሰው ዘር  አብነቶችን በሳይንሳዊ መንገድ አረጋግጠው ለማስተዋወቅ እየተጉ መሆናቸው ነው በድረገፆች ለንባብ የበቃው::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ደብሊው ኤች ሲ ዩኔስኮ፤ ቪዚት ኢትዮጵያ ትራቭል እና አፍሪካ  ዲስከቨሪን ተጠቅመናል::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here