የኦዞን መሸንቆርን የሚያባብሰዉ

0
123

ከሮኬት ማምጠቂያዎች የሚወጣው ጪስ እና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ የሳተላይት ስብርባሪዎች የሚለቁት በካይ ትነት በከባቢ ዓየር ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ሳይንስ ኒውስ ድረ ገጽ  ሰሞኑን  አስነብቧል፡፡

ለተለያዩ አገልግሎቶች ወደ ህዋ ተወንጭፈው ለተወሰነ ጊዜ አገልግለው ከጥቅም ዉጪ ሲሆኑ የሚተኩት ሳተላይቶች፣ በየዓመቱ ቁጥራቸው እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት የከባቢ ዓየር ተመራማሪው ዳኒኤል መርፊ በ”ኦዞን” ሽፋን ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ቢኖርም እስከአሁን በውል አለመታወቁን አስምረውበታል፡፡

በያዝነው ዓመት በመሬት ዙሪያ አስር ሺህ የሚጠጉ  ሳተላይቶች በህዋ ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

አገራት  በተናጠል ካመጠቋቸው መካከል ቻይና ባለፈው የነሐሴ ወር ብቻ 18 መላኳ  እና ቁጥራቸውን ወደ 12 ሺህ ለማድረስ ስለማቀዷም ነው የተጠቀሰው፡፡

በእስከአሁኑ የአገራት የሳተላይት የማምጠቅ ፍላጐት አንፃር በ2030 እ.አ.አ በምድር ዙሪያ መቶ ሺህ የሚደርሱ ሳተላይቶች ህዋን ሊያጨናንቁ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡

ለበየነ መረብ ግንኙነት የሚውሉ ሳተላይቶች ስሪታቸው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከአገልግሎት ውጪ ስለሚሆኑ ተሰባብረው  ህዋ ላይ ይቀራሉ፡፡ ከእነዚህ ስብርባሪዎች የሚለቀቁ ቅንጣቶችም  ወደ ከባቢ ዓየር ገብተው ብክለት እንደሚያስከትሉ ነው ተመራማሪዎች ያረጋገጡት፡፡

ተማራማሪዎቹ ሳተላይቶችን ለማስወንጨፍ ለሮኬቶች ከሚውል ኃይል ምንጭ ካርበን፣ ናይትሮጂን እና አልሙኒየም ኦክሳይድን የመሳሰሉ በካይ ትነቶች ሊለቀቁ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም ተመራማሪዎቹ ወደ ህዋ የሚላኩ ሳተላይቶች የሚያደርሱትን ተፅእኖ መገምገም እና ለአካባቢ ተስማሚ አማራጮችን መፈለግ ግድ መሆኑን ነው በማደማደሚያነት ያሰፈሩት፡፡፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here