የኦዲት ስራ ዉስን ጨረታ ማስታወቂያ

0
16

ዋን ኸርት ሆልነስ ሴንተር የበጎ አድራጎት ድርጅት በኢፌደሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ተመዝግቦ በምዝገባና ፈቃድ ቁጥር 5776 ህጋዊ ፈቃድ በማግኘት በኦቲዝም ሲፒ ኤንድ ዳዉን ሲንድረም ተጠቂ የሆኑ ህጻናትን እያገዘ እና እየተንከባከበ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ከነሀሴ 26/2014 ዓ/ም ጀምሮ ኦዲት እስከ ሚደረግበት ቀን ድረስ ያለዉን የበጀት አመቶች የድርጅቱን ሂሳብ በውጪ ኦዲተር ማስመርመር ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች  የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

  1. የኦዲተር የሙያ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
  5. ከፌዴራል ወይም ክልል ኦዲተር ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው
  6. ዋን ኀርት ሆልነስ ሴንተር ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች የጨረታዉ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ማመልከቻቸዉን በታሸገ ኢንቨሎፕ በአካል (በድርጅቱ ተወካይ ) ወ/ሮ ህሊና መንገሻ ስም በስልክ ቁጥር 09 43 37 53 70 በዲቸኤል ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች ዉል ከያዙ ጀምሮ ድርጅቱ በሚያወጣዉ የጊዜ ገደብ ሰርተው የሚያስረክቡ መሆን አለባቸው፡፡
  9. በማንኛውም  ደረጃ የሚገኝ ኦዲተር ማስታወቂያው  በጋዜጣ  በወጣ  በ 5 ቀናት  ውስጥ  የዋጋ   ማቅረቢያውን  በሰም  በታሸገ  ኤንቨሎፕ  በድርጅቱ  ዋና መ/ቤት ወይም በአካል ማቅረብ የማይችሉ ተወዳዳሪዎች በድርጅቱ ተወካይ ስም በዲኤችኤል መላክ የሚቻል መሆኑን ድርጅቱ ያሳውቃል፡፡

አድራሻ፡-ዋን ኀርት ሆልነስ ሴንተር ባህርዳር ቀበሌ 11፣ አባይ ማዶ ወደ ቤዛዊት ቤተመንግስት በሚወስደዉ መንገድ ከመስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሳይደርሱ ከመኪና ማጠቢያዎቹ ቀጥሎ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ  ስ.ቁ 09 43 37 53 70 ይደውሉ፡፡

ዋን ኸርት ሆልነስ ሴንተር የበጎ አድራጎት ድርጅት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here