የከሚሴ እናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
154

በወልድያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2016 በጀት ዓመት ለሚገነባው የከሚሴ እናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የሳይት ወርክ ሥራ እና የዋናው ብሎክ የብሎኬት ድርደራ ሥራ ሁሉንም ግብዓቶች በማሟላት መሥራት ለሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊና ብቃት ካላቸው ህንጻ ሥራ ተቋራጭ GC ደረጃ 5  እና በላይ የሆኑ ህንጻ ሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ህንጻ ሥራ ተቋራጮች  ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN /ሰርቲፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ። ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ጋራንቲዋና /ኦሪጂናል/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ቼክና ኢሹራንስ ማቅረብ አይቻልም/የተከለከል ነው። ተቀባይነት የለውም::
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ  የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ወልድያ ከተማ ጎማጣ በሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ:: የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን 11፡00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከጧቱ 4፡00  ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይታገድም::
  4. ክፍያን በተመለከት ኮንትራክተሩ በተሠራ ሥራ ልኬታ መሰረት በባለሙያ ሲረጋገጥ በአቅራቢዎች በንግድ ባንክ/ዓባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥራችው ገቢ ይሆናል::
  5. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ ጨምሮ መሙላት አለበት::
  6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው::
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የምሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 14 71 61 82/ 09 12 91 82 14 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

   የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here