- የጨረታ ዙር፡ የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ጨረታ
- የጨረታ አይነት፡- መደበኛ ጨረታ
- የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነገገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከተዘረዘረው መሠረት የመኖሪያ ቤት መስሪያ 18 /አስራ ስምንት/ ቦታዎች፣ ድርጅት ሆቴል 4 /አራት/፣ ድርጅት ሞንቴል 1 /አንድ/ በድምሩ 5 /አምስት/፣ የእህል ወፍጮ 1 /አንድ/ ናቸው፡፡ በጠቅላላ 24 /ሃያ አራት /ቦታዎች ናቸው፡
- በመደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ እንፈልጋለን፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 09/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ለመኖሪያ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለድርጅት ሆቴል፣ ለድርጅት ሞቴል፣ ለእህል ወፍጮ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በእን/ከተ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ከተ/መ/ል/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ቀን አስከ 11፡00 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሠነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ አስከ ተመዘገቡበት ቀን ድረስ በሥራ ስዓት ከቀኑ እስከ 11፡30 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ሠነድ ሽያጭ ባለቀበት ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ቦታዎች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በኋላ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም ከባለሙያ ጋር መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የመኖሪያ ቦታዎችና በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የድርጅት ሆቴል፣ የድርጅት ሞቴል እና የእህል ወፍጮ በእንጅባራ ከተ/አስ/አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 058 227 15 42 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት